ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ከ1000 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን በየጊዜው የአባላቱን ቁጥር እያሳደገ ያለ ሲሆን ለአባላት ምቹ አገልግሎትን በመስጠት አዳዲስ አባላት እያፈራ ያለ ተቋም ነው።በዚህም የአባላቱን ተጠቃሚነት እየጨመረ አሁን ካለው የአባላት ቁጥር በብዙ እጥፍ ይጨምራል።
አማዞን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር በኢ.ፌ.ዲ.ሬ. ኅብረት ሥራ ማህበራት ማቋቋሚያ አዋጅ 985/2009 መሠረት የተቋቋመ ህጋዊ ሰውነት ያለው ተቋም ነዉ። በዚህም በተሰጠው እውቅና እና ሀላፊነት መሰረት በአዲስ አበባና አካባቢ የሚገኙ የማህበረሰብ አባላትን፣ የመንግስት ሰራተኞችን እና የንግዱን ማህበረሰብ እንዲሁም ሌሎች የህብረተስብ ክፍሎች ያገለግላል።
የተመሰረተበትን አላማ ለማሳካት እና በሙሉ ኃላፊነት ለማከናወን ሰባት /7/ የቦርድ አመራር ኮሚቴ፣ በዋና ሊቀመንበር የሚመራ፣ እንዲሁም ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ማኔጅመንት ይስተዳድራል። አመራሩ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር የአባላቱን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፍላጎቶች ለማሟላት ዋና ተግባራትን ለማከናወን ከባለድርሻ አካላት ጋር በተገቢው መንገድ ይሰራል።
አማዞን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መሰ/የኅብረት ሥራ ማህበር ከተመሰረተ ጀምሮ ያሳየውን እድገትና ተፈጻሚ ውጤቶች በቁጥራዊ መረጃ
አባላት
የተሰራጩ ብድሮች
የአባላት ቁጠባ
የድርጅቱ ካፒታል
የሚከተሉትን መረጃዎች ተጠቅመው ለእርሶ የሚሆኖትን የብድር አምራጭ ይወስኑ እና ያትርፉ
ንግድዎን ከተወዳዳሪዎቹ ጎልቶ እንዲታይ የሚያደርጎትን እናቀርባለን።
ተበዳሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የብድር አገልግሎት ስለምናስገኝ
አጠቃላይ የመክፈያ መጠን በመቀነስ ብድሮችን ለመክፈል ቀላል ስለምናስገኝ
የግለሰብን የገንዘብ እና የግል መረጃ ደህንነት እና ጥበቃ ስለሚያረጋግጥ
ተለዋዋጭ ብድሮች ቀላል መዳረሻ እና ለስላሳ ተሞክሮ ስለምንሰጥ
ከኢስላማዊ ፋይናንስ ጋር የተጣጣመ ከወለድ ነፃ የሆነ የቁጠባ አማራጭ መስጠታችን
የተለያዩ የፋይናንስ ግቦችን ለማሟላት የተለያዩ የቁጠባ አማራጭ መስጠታችን
ከአገልግሎታችን ጋር ስላላቸው ልምድ ከደንበኞች የተሰጡ አስተያየቶችን፣ ግምገማዎችን ወይም ምስክርነቶችን ያሳያል
የተሳካ የብድር አሰጣጥ
የደንበኛ እርካታ ማረጋገጫ
ቢሮ ብሔራዊ አጋሮች
የሽልማት እና የምስክር ወረቀት
በቅርብ ጊዜ ያጋራናቸውን ዜናዎች እና ሁነቶች ይመልከቱ ሙሉንውን ለማየት ሙሉውን አሳይ የሚለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።
አማዞን ኃላ/ የተ/ ቁ/ ብ/ህ/ ሥራ ማህበር ከሀገር ውስጥ ባለፈ በዓለምእቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚው ዘርፍ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን ገለጸ አማዞን ኃላፊነቱ የተወሰነ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር በኅብረት ሥራ ጽንሰ ሀሳብ፣ በፋይናንስ አገልግሎትና ማርኬቲንግ እንዲሁም በሀገር አቀፍና ዓለማአቀፍ ተሞክሮዎች ላይ የጠራ አስተሳሰብ በመያዝ ለራዕዩ መሳካት በጋራ መንቀሳቀስ እንዲቻለው ከመላው ባለሙያዎቹና የስራ አመራር አባላቱ ጋር በጽንሰ ሀሳብና ተሞክሮዎች ላይ ዳሰሳና ምልከታ እያደረገ ነው : ማህበሩ ከሀገር ውስጥ ባለፈ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚው ዘርፍ የራሱን አስተዋጽኦ ለማበርከት ግዙፍ ራዕይ አንግቦ ዘርፉን እንደተቀላቀለ የተናገሩት የማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳሰና ዋና ሰፊ ስራ ለመስራት ብቃት ያላቸው ወጣት አመራሮችና የባለሙያዎች ስብስብ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ የፋይናንስ አገልግሎትን ዝቅተኛ ለሆነው የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ በወርሃ ጥር 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ደረጃ የተመሰረተው አማዞን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ በአነስተኛ ወለድ የመኪና፣ የቤት እና የአነስተኛ በዝነስ ስራዎች ብድርበማሰራጨት አባላቱን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ ለመኪና እና ቤት እስከ 2 ሚሊዮን እና ለአነስተኛ የቢዝነስ ስራዎች እስከ 500 ሺህ ብር የብድር ጣሪያ እያቀረበ ነው ያሉት ሥራ አስፈጻሚው በአጭር ጊዜ ከ90 በላይ ለሚሆኑ አባላቱ ብድር አመቻችቶ በራይድ ታክሲ ሥራና በአነስተኛ ቢዝነስ ተግባራት ውስጥ ገብተው የተሻለ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ አሰራሩን ወደኮር ባንኪንጊ ሲስተም እየቀየረ መሆኑን የጠቆሙት ሥራ አስፈጻሚው በቀጣይ ከባንኮችጋር ተመሳሳይሲስተም ለመጠቀም እና ተመሳሳይ ፕሮዳክቶች ለማቅረብ የማዘመን ስራ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አማዞን አባላትን ለማፍራት ቤት ለቤት እና በየድርጅቶች እየተንቀሳቀሰ እንደሚሰራ የጠቀሱት ሥራ አስፈጻሚው በየቀኑ ቢያንሰ 10 አባላት ማህበሩን እየተቀላቀሉ ነው ብለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ አማዞን በቦሌ ክፍለ ከተማ 22 ጎላጎል ጀርባ ከሚገኘው ኪያሜድ ኮለጅ ጎን ባለው ህንጻ 1ኛ ወለል ላይ ይገኛል ።