• ሃያሁለት, አዲስ አበባ
  • +(251) 948424344
  • amazonsaccos@gmail.com
  • UK FlagEnglish    UK FlagAmharic
ክአዲስ አበባ እስከ አለም አቀፍ፡ የአማዞን ህብረት ስራ ማህበር ደማቅ ራዕይ ለኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ

ክአዲስ አበባ እስከ አለም አቀፍ፡ የአማዞን ህብረት ስራ ማህበር ደማቅ ራዕይ ለኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ

  • 2025-05-08 13:31:43

አማዞን ኃላ/ የተ/ ቁ/ ብ/ህ/ ሥራ ማህበር ከሀገር ውስጥ ባለፈ በዓለምእቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚው ዘርፍ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን ገለጸ አማዞን ኃላፊነቱ የተወሰነ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር በኅብረት ሥራ ጽንሰ ሀሳብ፣ በፋይናንስ አገልግሎትና ማርኬቲንግ እንዲሁም በሀገር አቀፍና ዓለማአቀፍ ተሞክሮዎች ላይ የጠራ አስተሳሰብ በመያዝ ለራዕዩ መሳካት በጋራ መንቀሳቀስ እንዲቻለው ከመላው ባለሙያዎቹና የስራ አመራር አባላቱ ጋር በጽንሰ ሀሳብና ተሞክሮዎች ላይ ዳሰሳና ምልከታ እያደረገ ነው : ማህበሩ ከሀገር ውስጥ ባለፈ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚው ዘርፍ የራሱን አስተዋጽኦ ለማበርከት ግዙፍ ራዕይ አንግቦ ዘርፉን እንደተቀላቀለ የተናገሩት የማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳሰና ዋና ሰፊ ስራ ለመስራት ብቃት ያላቸው ወጣት አመራሮችና የባለሙያዎች ስብስብ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ የፋይናንስ አገልግሎትን ዝቅተኛ ለሆነው የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ በወርሃ ጥር 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ደረጃ የተመሰረተው አማዞን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ በአነስተኛ ወለድ የመኪና፣ የቤት እና የአነስተኛ በዝነስ ስራዎች ብድርበማሰራጨት አባላቱን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ ለመኪና እና ቤት እስከ 2 ሚሊዮን እና ለአነስተኛ የቢዝነስ ስራዎች እስከ 500 ሺህ ብር የብድር ጣሪያ እያቀረበ ነው ያሉት ሥራ አስፈጻሚው በአጭር ጊዜ ከ90 በላይ ለሚሆኑ አባላቱ ብድር አመቻችቶ በራይድ ታክሲ ሥራና በአነስተኛ ቢዝነስ ተግባራት ውስጥ ገብተው የተሻለ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ አሰራሩን ወደኮር ባንኪንጊ ሲስተም እየቀየረ መሆኑን የጠቆሙት ሥራ አስፈጻሚው በቀጣይ ከባንኮችጋር ተመሳሳይሲስተም ለመጠቀም እና ተመሳሳይ ፕሮዳክቶች ለማቅረብ የማዘመን ስራ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አማዞን አባላትን ለማፍራት ቤት ለቤት እና በየድርጅቶች እየተንቀሳቀሰ እንደሚሰራ የጠቀሱት ሥራ አስፈጻሚው በየቀኑ ቢያንሰ 10 አባላት ማህበሩን እየተቀላቀሉ ነው ብለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ አማዞን በቦሌ ክፍለ ከተማ 22 ጎላጎል ጀርባ ከሚገኘው ኪያሜድ ኮለጅ ጎን ባለው ህንጻ 1ኛ ወለል ላይ ይገኛል ።

መለያዎች
ብድር ልዩ ቀን